Search

ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት ላይ ትኩረት ተደርጓል ፦ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

ማክሰኞ ነሐሴ 20, 2017 108

ለዘመን መለወጫ ለነዋሪው ምቹ የገበያ አማራጭ በመፍጠር የምርት ፍላጎት እና አቅርቦትን ለማጣጣም እየተሰራ ነው ሲል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮ ኃላፊዋ ሀቢባ ሲራጅ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ መስከረም ወር አዲስ ዓመትን ጨምሮ በርካታ በዓላት እንደሚከበሩ አስታውሰው፤ ለነዋሪው ምቹ እና ተመጣጣኝ የግብይት ሥርዓት ለመፍጠር እንዲሁም የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቁም እንስሳት፣ ሰብል፣ የእንስሳት ተዋጽዖዎች፣ አልባሳት፣ የአትክልት ፍራፍሬ  እንዲሁም ሌሎች ምርቶችን ላይ የዋጋ ንረትም ሆነ እጥረት እንዳይፈጠር የከተማ አስተዳደሩ አቅርቦት ላይ እንሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በከተማዋ  500 በላይ ነጋዴዎች መኖራቸውን አንስተው፤  95 በመቶ የሚሆኑት የንግድ ሕጉን ተከትለው እንደሚሰሩ  ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

ያለአግባብ ዋጋ የሚጨምሩና ምርት የሚደብቁ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱንም አስታውቀዋል።

በተጨማሪ ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 5 ቀን ድረስ በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ባዛሮች እንደሚዘጋጁም ጠቁመዋል፡፡

ይህም ሸማቹ በአቅራቢያው እንዲሸምት እንደሚያግዝም ነው የተናገሩት።

 

በሜሮን ንብረት