በሲዳማ ክልል በተኪ ምርቶች ከ1.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ማዳን መቻሉን የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ገለፀ።
በክልሉ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ 1 ሺህ 300 አምራች ኢንዱስትሪዎች በግብርና፣ በጨርቃጨርቅ፣ በኬሚካል ውጤቶች እና በእንጨት ምርቶች ላይ ተሰማርተዋል።
በክልሉ የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም በማጠናከር ተኪ ምርቶችን ከማምረት ባለፈ ምርቶችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ 54 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱንም የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ለኢቢሲ ተናግረዋል።
በክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት የአምራች ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ተቋቁሞ እየተሠራ ሲሆን፤ አሁን ላይ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 61 በመቶ ላይ መድረሱን ቢሮው አስታውቋል።
በሲዳማ ክልል አምራች ኢንዱስትሪው ለአርሶአደሩ እና ለሌሎች ግብዓት አቅራቢዎች ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረ ሲሆን፤ በክልሉ ለኢንዱስትሪ ያሉ ዕድሎችን ለመለየት ሰፊ ጥናት እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።
በአስረሳው ወገሼ
#EBCdotstream #Sidama #Manufacturing #ImportSubstitution