በቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ የተመራ የልዑካን ቡድን በቼክ ሪፐብሊክ የሚገኘውን ኦምኒፖል የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጎበኘ።
በኦምኒፖል አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በተደረገው ጉብኝት ለቱሪዝም መዳረሻዎች የሚሆኑ ቱሪስቶችን ማጓጓዝ የሚያስችሉ አነስተኛ አውሮፕላኖችን መመልከታቸውንም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ የቱሪዝም መሰረተ ልማት ማሟላትን አላማ ያደረገ ምክክር እና ጉብኝት መካሄዱንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ ካሏቸው የትብብር መስኮች አንዱ የአቪዬሽን ዘርፉ መሆኑን አመላክተው፤ የዘመናት ትብብራቸውን ለማጠናከርም የሚረዳ ውይይት ተደርጓል ብለዋል።
በጉብኝቱም የአውሮፕላን አምራች ኩባንያው አመራሮች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል።
ኩባንያው በአቪዬሽን ዘርፉ ከ80 ዓመት በላይ ልምድ እንዳለው ተገልጿል።
በመቅደላዊት ደረጀ