የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው በዝቅተኛ የደመወዝ ስርዓት ውስጥ ያሉ ዜጎችን በይበልጥ ተጠቃሚ ያደረገ እና የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል ያለመ መሆኑን የምጣኔ ሀብት መምህር እና ተመራማሪው ገልጸዋል፡፡
በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር እና ተመራማሪው መሀመድ ኢሳ (ዶ/ር) ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ አንድ አካል የሆነው የገቢ ግብር አዋጅ አነስተኛ ደመወዝ ያላቸው ዜጎች ጫና ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ለዚህም ማሳያ ብለው ያቀረቡት ከዚህ ቀደም የነበረው ከ6 መቶ ብር በላይ የሆኑ ተከፋይ ሠራተኞች ግብር የሚቆረጥባቸው የነበረ ሲሆን በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ግን ከ2 ሺህ ብር በላይ ደመወዝ ተከፋይ የሆኑ ዜጎችን እንዲያካትት መደረጉን ነው ያነሱት፡፡
ይህም አነስተኛ ደመወዝ ያላቸው ዜጎች ጫና ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ የታሰበ ስለመሆኑ የጠቀሱት መምህሩ ይህ ሲሆን መንግሥት የሚያጣው ነገር ቢኖርም ለዜጎቹ ያለውን ቁርጠኝነት ግን እንደሚያሳም ነው የጠቀሱት፡፡
በሜሮን ንብረት