2ኛው ሀገር አቀፍ “የኢትዮጵያን ይግዙ” የንግድ ሳምንት ኤክስፖ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ካሳሁን ጎፌ እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተከፍቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮን ጨምሮ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ160 በላይ የንግድ ድርጅቶች እና አምራቾች የሚሳተፉበት ኤክስፖው፤ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የውጭ የኢኮኖሚ ተጋላጭነትን የሚቀንስ ስለመሆኑ ተገልጿል።
የንግድ ሳምንቱ የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎት ለማስተዋወቅና ለማበረታታት፣ የገበያ ትስስር እና የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ የላቀ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።
ኤክስፖው ከዛሬ ነሐሴ 24 እስከ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
በብሩክታዊት አስራት
#EBCdotstream #ETV #Ethiopia #TradeWeek #BuyEthiopian