Search

ዓባይ ባንክ እና ቪዛ የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ለማፋጠን የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረሙ

ቅዳሜ ነሐሴ 24, 2017 59

ዓባይ ባንክ እና ቪዛ ኢትዮጵያ ያደረጉት የስትራቴጂ ትብብር ስምምነት ባንኩ የኢትዮጵያን ዲጂታል ሽግግር ለማገዝ የሚረዱ የቪዛ አገልግሎቶችን ማስጀመር የሚያስችለው ነው።

በዓባይ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ስምምነቱን የተፈራረሙት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የኋላ ገሠሠ እና የቪዛ ኢትዮጵያ ሀላፊ ያሬድ እንዳለ ናቸው።

ስምምቱ ዓባይ ባንክ ደኅንነታቸው የተጠበቀ፣ ምቹ እና ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የክፍያ መፍትሄዎችን እና የቪዛ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ ማቅረብ የሚያስችለው ነው።

የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን ለመግታት እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በዲጂታል ኢኮኖሚው እንዲሳተፉ ለማስቻል የሚደረገው ሰፊ እንቅስቃሴ አካልም ነው።

ትብብሩ ዓባይ ባንክ የቪዛ ዓለም አቀፍ መረብን እና እጅግ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ሀብቶች በመጠቀም ለግል እና ለንግድ ቀልጣፋ የክፍያ አገልግሎት እንዲያቀርብ ይረዳል።

የዓባይ ባንክን የሀገር ውስጥ ሰፊ ተደራሽነት ከቪዛ ዓለም አቀፍ ልምድ ጋር በማቀናጀት ኢትዮጵያ ከጥሬ ገንዘብ ዝውውር ነፃ ወደ ሆነ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ለማፋጠን ስምምነቱ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

በተጨማሪ ስምምነቱ የዲጂታል ፋይናንስ ክህሎቶች እና አገልግሎቶችን ተደራሽ ወዳልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የማስፋት የጋራ ሥራዎችን እንድሚያካትትም ነው የተገለፀው።

በኤዶምያስ ንጉሴ

#EBCdotstream #ETV #AbayBank #VISA #Agreement