Search

በቀን ከ300 በላይ ዘመናዊ የብረት በሮችን የሚያመርተው ፋብሪካ

ቅዳሜ ነሐሴ 24, 2017 53

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚተዳደረው የኮምቦልቻ ብረታ ብረት ምርቶች ኢንዱስትሪ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በገላን ከተማ ያስገነባው የብረት በር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ።

ፋብሪካው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጀማል አህመድን ጨምሮ የሸገር ከተማ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች እና የፋብሪካው ሀላፊዎች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

ፋብሪካው በቀን ከ300 በላይ ዘመናዊ የብረት በሮችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል።

ፋብሪካው አሁን ላይ ከ150 በላይ ለሆኑ የአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል ተብሏል።

በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባም በጥቅሉ ከ250 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተመላክቷል።

በአሚር ጌቱ

#EBCdotstream #ETV #MIDROC #KOSPI