የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
ኮርፖሬሽኑ ይህን ያስታወቀው የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው።
የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው፥ በበጀት ዓመቱ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኮንትራት ዋጋ ያላቸው 34 ፕሮጀክቶችን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ገንብቶ ማስረከቡን ገልጸዋል።
አሁንም ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ የኮንትራት ዋጋ ያላቸው 28 አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክት ዕቅዶችን ተረክቦ በግንባታ ላይ እንደሚገኝ ነው የጠቆሙት።
ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ የዕቅዱን 102 በመቶ ማከናወን መቻሉን የገለፁት ሥራ አስፈጻሚው፤ ተቋሙ የአፈጻጸም አቅሙን በ92 በመቶ እንዳሳደገም ጠቁመዋል።
ኮርፖሬሽኑ በርካታ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የውጭ እና የውስጥ ደንበኞች እንዳሉት ጠቅሰው፤ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት መሠረት በበጀት ዓመቱ የደንበኞች የእርካታ ደረጃን 88.3 በመቶ ማድረስ እንደቻለ አስታውቀዋል።
ኮርፖሬሽኑ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የጀመራቸውን የልህቀት ዕቅዶች ተግባራዊ በማድረግ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር በርካታ ተግባራት ማከናወን መቻሉ ተገልጿል።
በወንድማገኝ ኃይሉ
#EBCdotstream #ETV #ECC #Performance #Projects