በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሂደት አስመልክቶ የወላይታ ዞን አስተዳደር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ተሰማ በመግለጫቸው፤ በዞኑ በፌደራልና በክልሉ መንግሥት የተጀመሩ በርካታ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን አመላክተዋል።
ከኮንትራክተር እንዲሁም ከካሳ እና ወሰን ማስከበር ጋር የተያይዙ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
መሰል ችግሮች ከሚታዩባቸው ፕሮጀክቶች መካከል የወይቦ መስኖ ፕሮጀክቶች፣ የአየር ማረፊያ እና የከተማ አስፓልት መንገድ እንደሚጠቀሱ አንስተዋል።
የፕሮጀክቶቹን ግንባታ ለማፋጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለልማት ተነሺዎች ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ እንደሚከፈል ጠቁመዋል።
በተመስገን ተስፋዬ
#EBC #ebcdotstream #infrastructure
ለልማት ተነሺዎች ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ በመክፈል የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ይሰራል - የወላይታ ዞን አስተዳደር
ቅዳሜ ነሐሴ 24, 2017 43
