የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዳያስፖራ ማኀበረሰብ ብድር አገልግሎት የሚውል 50 ቢሊዮን ብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
በባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ የተመራው ልዑክ በዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የተለያዩ ከተሞች የሥራ ጉብኝት በማድረግ በዚያ ከሚገኙ የዳያስፖራ ማኀበር አካላት ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል።
ባንኩ ለኢቢሲ በላከው መረጃ እንዳመላከተው፤ በውይይቱም ለዳያስፖራው ማኀበረሰብ ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለቤት እና መኪና ግዥ የሚውል 50 ቢሊዮን ብር ብድር ባንኩ ማዘጋጀቱን ተገልጿል።
የዳያስፖራውን ማኀበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግበት አሰራር ባንኩ ከጀመራቸው ሰፊ የለውጥ ሥራዎች መካከል አንዱ መሆኑ ተመላክቷል።
በሜሮን ንብረት