በ2017 በጀት ዓመት 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች በኢትዮጵያ የተለያዩ የመዳረሻ ስፍራዎችን መጎብኘታቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
“በተናበበ እቅድ የሰመረ ተግባር፣ ለቱሪዝም ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ የ2017 በጀት ዓመት የቱሪዝም ዘርፍ አፈፃፀም እና የ2018 ዕቅድ ላይ ያተኮረ ጉባዔ በጅግጅጋ ተካሂዷል።
በመድረኩ ቱሪዝም ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 2.7 በመቶ ድርሻ እንዳለው ተመላክቷል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፤ በ2017 በጀት ዓመት የፖሊሲ ክለሳ በማድረግ ውጤታማ ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል።
በ2018 በጀት ዓመት ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ የሚኖረውን አስተዋፅዖ ለማላቅ በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል።
በመድረኩ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሀመድ፤ በክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ በተለይ በሆቴል ቱሪዝም መነቃቃት መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
በክልሉ የጎብኚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መንግሥት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#EBC #ebcdotstream #landoforigins