Search

ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁን በማስመልከት በጋምቤላ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው

ቅዳሜ መስከረም 03, 2018 65

በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን በማስመልከት ነዋሪዎች የተሰማቸውን ደስታ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለፁ ይገኛል።
ነዋሪዎቹ የግድቡ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁ የኢትዮጵያውያንን ፅናት እና ጠንካራ አንድነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
 
በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች በርካታ ጫናዎችን ተሻግሮ በኢትዮጵያውያን የጋራ ተሳትፎ እውን የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፅናታችን እና የአንድነታችን ውጤት ነው በማለት ገልፀዋል።
የግድቡ መጠናቀቅ በጋራ ጠንክረን ከሰራን ለድል መብቃት እንደሚቻል ያረጋገጥንበትም ነው ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ የዘመናት ቁጭት እና ህልማችን እውን መሆን የቻለበትም ፕሮጀክት ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ በክልሉ በቀጣዮቹ ቀናትም የተለያዮ መርሀ ግብሮች እንደሚከናወኑ ተጠቁሟል።
 
በሚፍታህ አብዱልቃድር