Search

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጁነታቸውን አረጋገጡ

ዓርብ ጥር 29, 2018 61

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሻለ ሃሳብ በመያዝ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ገለጹ።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከለውጡ በኋላ በተዘረጋው አሳታፊ ምኅዳር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከመንግሥት ጋር በመቀናጀትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በመመደብ አዲስ የፖለቲካ አውድ መፍጠር መቻላቸውን ገልጸዋል።
በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የዲጂታል አገልግሎት አማካኝነት እየመዘገቡ መሆኑን አቶ ተስፋሁን ገልጸዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ በትኩረት እንደሚሠራም አስታውቀዋል።
ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣም አስገንዝበዋል።
 
በተስፋሁን ደስታ