Search

ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክቱን ይፋ አደረገ

ማክሰኞ የካቲት 03, 2018 132

ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክቱን ይፋ አድርጓል።
ብልፅግና የምርጫ ማኒፌስቶውን እና የምርጫ ምልክቱን ይፋ ያደረገው የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ተመስገን ጥሩነህ፣ የፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ እንዲሁም የፓርቲው አመራሮች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው።
ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወከልበት የምርጫ ምልክቱ የስንዴ ነዶ መሆኑን አስታውቋል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት በ6ኛው ምርጫ እና በ7ኛው ምርጫ መካከል ብልፅግና ፓርቲ እውን ያደረጋቸውን ሁለንተናዊ ስኬቶች በንፅፅር አቅርበዋል።
መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው ሪፎርም ኢትዮጵያን ከዕዳ ወደ ምንዳ ያሸጋገረ እና ዓለም አቀፍ እውቅና የተቸረው መሆኑን ተናግረዋል።