የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የታላቁ ሕዳሴ ግድባችን የ14 ዓመት ጉዞ፤ በተለይም የሕዝቡን ተሳትፎ የሚያሳይ የፎቶ፣ የስዕል እና በዓባይ ዙሪያ የተፃፉ መፃሕፍት አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት አካሂደናል ብለዋል።

በፖናል ውይይቱ የሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ያለዉ ፋይዳ፣ ከጂኦስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና መሸጋገር፣ የሕዝብ አንድነትና ተሳትፎ ትርጉም አስመልክቶ በምሁራን ትንታኔ ቀርቧል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባለፉት 14 ዓመታት ያለፈበት ውጣ ውረድ፣ የተገኙ ድሎች፣ የውሃ ፖለቲካ ምንነት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል።