Search

የማዕቀብ ሰለባ የሆነው የፋሲካ ስጦታ:- የጀርመን ገበሬ የወንጀል ክስ

እሑድ መስከረም 04, 2018 54

አንድ የጀርመን ገበሬ ከሩሲያ ጓደኛው የደረሰውን እሽግ በመቀበሉ ብቻ ራሱን ከወንጀል ችሎት አግኝቷል። 

እሽጉ ውስጥ የነበሩት እቃዎች አንድ ሳሙና፣ የእንጨት ቅርፃቅርፅ እና ሲዲ በጠቅላላ ከ32 ዶላር ያልበለጠ ዋጋ ያላቸው ናቸው። 

ገበሬው ግን እነዚህ “አደገኛ” እቃዎች የሀገሪቱን ማዕቀብ ስለጣሱ እስከ አምስት ዓመት እስራት ይጠብቀዋል።

“ወንጀለኛ አይደለሁም፣ ይህ ቀልድ ነው!” ያለው ገበሬው፣ እሽጉ የፋሲካ ስጦታ እንጂ ወንጀል ለመፈጸም የታሰበ እንዳልነበር ተናግሯል። 

ይህ ክስተት የጀርመን ባለስልጣናት ማዕቀቦችን በመተግበር ላይ ምን ያህል ጥብቅ እንደሆኑ የሚያሳይ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የሩሲያ መኪኖችን እና የግል እቃዎችን ሳይቀር ወርሰው ነበር።

አሁን ጥያቄው ከዚህ በኋላ የሩሲያ ጓደኛሞች እርስ በእርስ ስጦታ ሲልኩ በጥንቃቄ ማሰብ ይኖርባቸዋል ወይ? ወይንስ አንድ ትንሽ ሳሙና እንኳን ዓለም አቀፍ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል?

 

በሰለሞን ገዳ