Search

የአንድነት እና የፅናት ምሳሌ የሆነው ሕዳሴ የፈጠረው ደስታ

ሰኞ መስከረም 05, 2018 24

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለምርቃት መብቃቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ በሰንደቅ አላማ ታጅበው የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል። ደስታቸውንም በአደባባይ ገልጸዋል።
በዚሁ ሁነት ላይ የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ኢትዮጵያ ያሰበችውን ማሳካት ትችላለች እኛም ደስታችንን ከልጆቻችን ጋር አክብረናል ሲሉ ገልጸዋል።
በድጋፍ ሰልፉም የሕዳሴ ግድብን መገንባት አትችልም የተባለችው ኢትዮጵያ እንደምትችል ለዓለም ማሳየቷ ለእኛ ኩራት ሲሉ የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል።
ኢትዮጵያ ብዙ መከራ እና ችግሮችን በማለፏ የፅናት እና የአይበገሬነት ምሳሌ መሆኗን ማሳየት እንደቻለች ነው ነዋሪዎቹ የጠቀሱት።
ግድቡ የአንድነታችን ገመድ ሆኖ እና እርስ በእርስ እንድንተባበር እና እንድንተሳሰብም አድርጎናል ሲሉም ገልፀዋል።
ግድቡ ከልማት ፕሮጀክትነት ባለፈ አንድነት ያለውን ኃይል አሳይቶናል ሲሉም ተናግረዋል።
መጪው ትውልድ ፅናት እና ጥንካሬን በመማር የራሱን ድል ማስመዝገብ ይገባዋል ብለዋል ነዋሪዎቹ።
 
በሜሮን ንብረት