Search

ስንተባበር ብዙ መልካም ነገሮችን ማድረግ እንችላለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እሑድ መስከረም 11, 2018 50

ስንተባበር ብዙ መልካም ነገሮችን ማድረግ እንችላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

በአዲስ አበባ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ ከ 1 ሺ 600 በላይ ቤቶች ለአገር ባለውለታዎች፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ተላልፈዋል፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ስንተባበር ብዙ መልካም ነገሮችን ማድረግ እንችላለን ብለዋል፡፡

ቤቶቹ የህፃናት መጫዎችን፣ የስፓርት ማዘዉተሪዎችን የያዙ እና በአጠቃላይ አብሮነትን  እና ጉርብትናን የሚያጠናክሩ መሆናቸው ተገልጿል።

በምንተስኖት ይልማ