በ2018 በጀት ዓመት በ4 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴን ለማልማት መታቀዱን የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ ገለፁ።
የኦሮሚያ መስኖ እና አርብቶ አደሮች ልማት ቢሮ ለበጋ መስኖ እርሻ የሚያግዙ የተለያዩ የውኃ መሳቢያ ፓምፖችን ለአርሶ አደሩ አስረክቧል።
የውኃ ፓምፖች ስርጭቱም ለተያዘው የግብርና ልማት ዕቅድ መሳካት አጋዥ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ።
የኦሮሚያ ክልል የመስኖና የአርብቶ አደሮች ልማት ቢሮ ኃላፊ ግርማ ረጋሳ (ኢ/ር) በበኩላቸው፤ በ2018 በጀት ዓመት 26 ሺ 166 የውኃ መሳቢያ ፓምፖችን ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሔክታር መሬትን በመስኖ ለማልማት መታቀዱን ገልፀዋል።
ክልሉ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 3 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ ለማከናወን ማቀዱን አንስተዋል።
የውኃ መሳቢያ ፓምፖች ርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተለያዩ የፌዴራል እና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አስማረ ብርሃኑ
#EBC #ebcdotstream #Agri #mechanization