Search

የመደመር መንግሥት ትልቁ ትኩረት የሀገሪቱን ዕጣ ፋንታ ለባለቤቱ ማስረከብ ነው

ረቡዕ መስከረም 14, 2018 63

የመደመር መንግሥት ትልቁ ትኩረት የሀገሪቱን ዕጣ ፋንታ እና ራዕይን ለኢትዮጵያውያን ማስረከብ ነው ሲሉ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዲቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ገመቺስ መርሻ (ዶ/ር) ገለጹ።
ዶ/ር ገመቺስ ከኢቲቪ የአዲስ ቀን መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ “የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ሁለንተናዊ መሻት ሀገራችን ካለችበት ነባራዊ ሁኔት እና ከነበርንበት ስብራቶች አንጻር ከፍ ያለ ሐሳብ ያለው ነው” ብለዋል።
የመደመር መንግሥት መጽሐፍ እንደ ፍልስፍና ያስቀመጣቸው ጉዳዮች ከሐሳብ ባሻገር በተግባር እየታዩ ስለመሆናቸውም አንሥተዋል።
ለነገሮች ፍጥነት እንደሚያስፈልግ የሚያትተው መጽሐፉ፣ ይህም በሀገሪቷ በሚሠሩ በፕሮጀክቶች በተግባር የታየ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ያሉ ችግሮችን በመለየት ከዚህ እንዴት መውጣት እንደሚቻል የሚያመልክት እንደሆነም ነው የገለጹት።
የመደመር መንግሥት በዚኮኖሚው ዘርፍ፣ በገበያ መር ኢኮኖሚ እንደሚያምን እንዲሁም አዋጭነቱን እንደሚያስረዳ ጠቅሰዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ተከታታይነት ያለው ዕድገት ስለመመዝገቡ ዶክተር ገመቺስ ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት የዓለም ኢኮኖሚ በተለያዩ ምክንያቶች መንገጫገጩን አስታውሰው፣ በኢትዮጵያ የተተገበረው የማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ገበያው እንዲረጋጋ ስለማስቻሉም ይጠቅሳሉ።
የዓለማች ትልቅ የስንዴ አምራች የሆኑ ሀገራት በጦርነት ክፉኛ ተጎድተው ነበር፤ ኢትዮጵያም ከነሱ ብቻ ስንዴ ብትጠብቅ ኖሮ ከባድ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ልትገባ ትችል ነበር ሲሉ ነው ያስረዱት።
በኢትዮጵያ መሬት ጾሙን ያድር እንነበረ እና በለውጡ መንግሥት ውኃ እና የሰው ኃይል ወደ ሥራ በማስገባት ሀገሪቱ በራሷ አቅም እንድታመርት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ከራሷ አልፋ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መጀመሯን ነው ያነሡት።
"ከጎረቤት ሀገር ያመጣነው መሬት እና ውኃ የለም" የሚሉት የዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ መምህሩ፣ የነበሩ ግን ያልተጠቀምናቸውን ሀብቶች በመጠቀም ታሪክ ሊሠራ ችሏል ብለዋል።
“አሁንም ቢሆን ተከፋፍለን በአፍራሽ መንገድ ከተጓዝን ዳግም ዓለም ጥሎን ይሄዳል፤ የውስጥ አቅምን ለመፍጠር የወል ትርክት ያስፈልገናል” ምክራቸውን ለግሰዋል።
በሜሮን ንብረት