Search

"ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን አጠናቅቃ በመመረቋ እንኳን ደስ አላችሁ!" - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

ሓሙስ መስከረም 15, 2018 55

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አጠናቅቃ በመመረቋ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በተጨማሪም ሀገሪቱ የአየር ንብረት ጉባኤን እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በማስተናገድ ላስመዘገበችው ስኬት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከዋና ጸሐፊው ጋር በቀጣናው እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።