Search

የሕዳሴ ሌላኛው የኢኮኖሚ ትሩፋት - ንጋት ሐይቅ

እሑድ መስከረም 18, 2018 84

"ዓባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል" የሚለው ተረት ተቀይሯል፤ ወንዙም ማደሪያ አግኝቶ የሥራ ዕድልም እየፈጠረ ይገኛል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፈጠረው ንጋት የሰው ሰራሽ ሐይቅ በውስጡ በርካታ የዓሣ ዝርያዎችን ይዟል ይላሉ በአካባቢው ጥናት ያደረጉ።
በዓሣ በማጥመድ እና በንግድ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ደግሞ በግድቡ አማካኝነት የተፈጠረው ንጋት ሐይቅ ከዕለት ጉርስ ባለፈ ተጨማሪ ገቢም ፈጥሮልናል ይላሉ።
በዓሣ ማስገር ሥራ ላይ የተሰማሩት ወጣቶቹ በየዕለቱ የተለያየ ዓይነት ዝርያ እና ክብደት ያላቸውን ዓሣዎችን እንደሚያገኙ ይገልፃሉ።
ንጋት ሐይቅ በፈጠረላቸው ትሩፋት ደስተኞች እንደሆኑ እና ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች በኢኮኖሚ መትረፋቸውን ይናገራሉ።
ሐይቁ ለዓሣ ሃብት ልማት እና ለኢኮኖሚው የፈጠረው መነቃቃት ከፍተኛ ነው ይላሉ።
 
በሄለን ተስፋዬ