የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት በአዲስ አበባ በስካይላይት ሆቴል ከዛሬ መስከረም 20 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ሁነቶች መካሄድ ጀምሯል።
መርኃ ግብሩን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አብዱላዚዝ ዳውድ (ዶ/ር) አስጀምረውታል።
ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው የቱሪዝም ሳምንት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና ባህላዊ ትውፊቶችን የሚያስተዋውቁ አውደ-ርዕዮች ቀርበዋል።
በቱሪዝም ሳምንቱ የተለያዩ የውይይት መድረኮች፣ የኦሮሚያ ቱሪዝም ሽልማት፣ የቁንጅና ውድድር እና ሌሎች መሰናዶዎች ይካሄዳሉ ተብሏል።
በሞላ ዓለማየሁ
#EBC #ebcdotstream #Irreecha #Tourism