Search

የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለ3 አገልግሎት አቅራቢዎች ፍቃድ ሰጠ *******

ረቡዕ መስከረም 21, 2018 14

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለ3 አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት አቅራቢዎች ፍቃድ መስጠቱን አስታወቀ።
በዚህም መሰረት ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ እንዲሁም ኢግናይት ካፒታል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሰነደ መዋዕለንዋይ ኢንቨስትመንት ማማከር ዘርፍ ፈቃድ አግኝተዋል ተብሏል።
በተጨማሪም ዙሪ ካፒታል አክሲዮን ማኅበር ሰነደ መዋዕለንዋይ ኢንቨስትመንት ማማከር ዘርፍ ፈቃድ ማግኘቱ ተጠቁሟል።
ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከባንክ ግሩፕ ውጪ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው የኢንቨስትመንት ባንክ መሆኑ ተመላክቷል።
ፍቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ኢትዮጵያ በጀመረችው አካታች እና ሁሉን አቀፍ የካፒታል ገበያ ስርዓት ግንባታ ላይ ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁ አሳስበዋል።
በባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ቁጥር ከስምንት ወደ አስራ አንድ ከፍ ማለቱም ተገልጿል።
 
በብሩክታዊት አስራት