Search

4ኛው የአፍሪካ ፋክትስ ሳሚት በሴኔጋል እየተካሄደ ነው

ሓሙስ መስከረም 22, 2018 125

ከ20 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ከ200 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙበት 4ኛው የአፍሪካ ፋክትስ ሳሚት በዳካር፣ ሴኔጋል እየተካሄደ ይገኛል።

በአፍሪካ ቼክ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ ጋዜጠኞች፣ ተመራማሪዎች፣  የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች እና ፖሊሲ አውጭዎች ተገኝተዋል።

በእውነታ ላይ የተመሠረተ አስተማማኝ መረጃ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተፅዕኖ፣ የተቀናጀ አሠራር አማራጮች እና የሐሰተኛ ዜና ተጋላጭነት የጉባኤው ዋነኛ አጀንዳዎች ናቸው። 

በጉባዔው በአፍሪካ ውስጥ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመከላከል ረገድ ያሉ ዕድሎች እና ፈተናዎችን በተመለከተ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ጉባዔው በአህጉሪቱ ባለው የመረጃ ታማኝነት ሥነ-ምህዳር ውስጥ ያሉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ ፕሮጀክቶችን እና በእውነታ ማጣራት ሂደት ውስጥ ያሉ ዕድገቶችን የሚዳስስ ይሆናል።

ጉባዔው በፋክት ቼክ ለውድድር ከቀረቡ የዓመቱ የሐሰተኛ መረጃ ማጣራት ሥራዎች መካከል ለአሸናፊዎች እውቅና እና ሽልማት በመስጠት ይጠናቀቃል።

በሴራን ታደሰ

#EBCdotstream #Africa #factcheck #factchecksummit