Search

ኢሬቻ እርቅ እና ሰላም የሚጎላበት የምስጋና በዓል ነው - አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች

ሓሙስ መስከረም 22, 2018 38

ኢሬቻ ፈጣሪ ክረምቱን ከመጥፎ ነገሮች ጠብቆ በሰላም አሻገረን በማለት የሚከበር የምስጋና በዓል መሆኑን ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ተናግረዋል።
ኢሬቻ በመተሳሰብ መንፈስ የሚከበር በመሆኑ የተጣሉ ሰዎች በአጋጣሚ በዓሉ የሚከበርበት ስፍራ ላይ ቢገናኙ እንኳን ታርቀው በጋራ የሚያከብሩት በዓል መሆኑን አንስተዋል።
ኢሬቻ አንድነትን የሚያንፀባርቅ በዓል ነው ያሉት አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች፤ በዓሉ የርስ በርስ ትስስርን በማጠናከር አብሮነትን ለማጉላት ከፍተኛ ሚና እንደአለው ገልጸዋል።
ኢሬቻ ሁሉም ዜጋ ያለምንም ልዩነት የሚሳተፍበት የፍቅር በዓል መሆኑንም አመላክተዋል።
 
የአሁኑ ትውልድ እንደ ኢሬቻ ያሉ ማኅበራዊ እሴቶችን መጠበቅ እና ማሳደግ ይገባዋል ብለዋል።
 
በቢታኒያ ሲሳይ