ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥት ደረጃ ሙስና ምንም ዓይነት ቦታ የለውም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ባለሀብቶች አንድም ብር ባልተገባ መንገድ ላልተገባ ሰው እንዲያውሉ የሚያደርግ ሁኔታ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የውጭ ባለሀብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉት ገንዘብ ለሀገራዊ ዓላማ ብቻ ይውላል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈስሱ የውጭ ባለሀብቶችን መንግሥት በንፅህና ለማገልገል ቁርጠኛ መሆኑንም ዳግም አረጋግጠዋል።
መንግሥት በሶማሊ ክልል የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ላይ ለሚሰሩ ባለሀብቶች ከሙስና የፀዳ ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ለማስደሰት ዝግጁ መሆኑንም ነው በመልዕክታቸው የገለፁት።
ፕሮጀክቱ አሁን ለደረሰበት ደረጃ በከፍተኛ ቁርጠኝነት ለሰሩ ለፌደራል ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ ለሶማሊ ክልል ሕዝብ እና ለክልሉ አስተዳደርም ምስጋና አቅርበዋል።
በላሉ ኢታላ