ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ምርቃት እና ሁለተኛ ዙር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውንም በነዳጅ የሚሰራ ትራክ ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት የተከለከለ ነው ብለዋል።
በአንፃሩ ማንኛውም ባለሀብት ጋዝ የሚጠቀሙ ቦቴዎች እና ከባድ ተሽከርካሪዎችን የሚያስገባ ከሆነ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት አስታውቀዋል።
በአንድ ጊዜ ውስጥ 2 ሺህ የሚጠጉ ወደአዲስ አበባ ከተማ እና ወደ ክልል የሚሄዱ ባሶች አሁን ከሚጠቀሙት ነዳጅ ወደ ጋዝ እንቀይራለን ብለዋል።
ወደ ሁለት ሺህ መኪናዎች ወደ ጋዝ ሲቀየሩ የትራንስፖርት ዋጋ ቢበዛ ወይም ቢያንስ አሁን ካለው ግማሽ በመቶ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚቀንስ ገልጸዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ