የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ማማታ ሙርቲ ጋር በሰው ሃብት ልማት ላይ ያለውን አጋርነት ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።
ሚንስትሩ በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት፣ ለጤና አገልግሎት መሻሻል፣ የጨቅላ ህጻናት እና የእናቶች ሞትን ለመቀነስ እንዲሁም ለሴፍቲኔት ድጋፍ ቅድሚያ ትኩረት መስጠቷን ገልጸዋል።
የዓለም ባንክ በሰው ሃብት ልማት፣ በሴፍቲኔት፣ በትምህርት፣ በሥራ ክህሎት እና በጤና አገልግሎት ዘርፎች ላደረገው ያልተቋረጠ ድጋፍም አመስግነዋል።
የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ማማታ ሙርቲ በበኩላቸው፥ ባንኩ አሁንም በተለይ በጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
#EBCdotstream #Ethiopia #MoF #WorldBank