Search

ባህርዳር እንደ መስከረም ንጋት ውበት፣ ተስፋ እና ልማት ሆኖላታል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ሰኞ መስከረም 26, 2018 70

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፥ ባህርዳር እንደ መስከረም ንጋት ውበት፣ ተስፋ እና ልማት ሆኖላት ተመልክተናል ብለዋል።

አክለውም ውኃ ከነውበት እና ስክነቱ፤ መልክዓ ምድር ከነ ለምነቱ፤ ልምላሜ ከነ ንጹህነቱ የታደለችው የውበት ምልክቷ  ባህርዳር፤ በጠንካራ አመራርና ነዋሪዎች የጋራ ጥረት ውበቷ ይበልጥ እየፈካ እና  እየደመቀች ነው ሲሉ ምልከታቸውን ገልጸዋል።

በግዙፉ ዓባይ ላይ የተገነባው ባለግርማው ድልድይ ለባህርዳር ከድልድይም በላይ መለያ ቀለሟ፣ የቱሪዝም መዳረሻዋ መሆኑን ተመልክተናልም ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

"ባህርዳር ውበቷን እና ክብሯን የሚመጥኑ የመናፈሻ ስፍራዎች እየተገነቡ፤ የኮሪደር ልማቱም ከውበት የተሻገረ ልማት አሳላጭ ሆኖ በፍጥነት እና ፈጠራ እሴቶች እያማረች ነው" ሲሉም የከተማዋን ዕድገት ገልጸዋል።

የብልጽግና ጉዟችን መዳረሻም እንደሀገር ወደሚመጥነን ከፍታ መሸጋገር ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።