Search

“የተፈጥሮ ጋዝ ለአፈር ማዳበሪያ ምርት ትልቅ ግብዓት ነው”

ሰኞ መስከረም 26, 2018 34

የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ እንዲሁም የፕራግማ አማካሪ ድርጅት መስራች እና ዋና አስፈፃሚ የሆኑት መርዕድ ብስራት፥ የተፈጥሮ ጋዝ ለአፈር ማዳበሪያ ምርት ትልቅ ግብዓት እንደሆነ ገልጸዋል።

በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን በሶማሊ ክልል፣ ኦጋዴንካሉብ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት በቅርቡ ግንባታው ለተጀመረው የጎዴ አፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ዋነኛ ግብዓት እንደሚሆን ተናግረዋል።

ይህም ገበሬው በቂ የአፈር ማዳበሪያ እንዲያገኝ እና ምርታማነት እንዲያድግ በማድረግ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል እያከናወነችው ያለውን ዘርፈ ብዙ ሥራ ያሳልጠዋል ሲሉ ገልጸዋል።

በጥቅሉ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ እነዚህ እና ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶች ኢንቨስትመንት በመሳብ፣ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ገቢ ምርቶችን በመተካት ጉልህ አስተዋፅዖ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

#ebcdotstream #ethiopia #calub #naturalgas #gode #fertilizer