Search

የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል መንግሥት በትኩረት ይሠራል - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ

ሰኞ መስከረም 26, 2018 31

መንግሥት ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ እና የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሠራ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ገልጸዋል።

መንግሥት ባለፉት ዓመታት ጠንካራ የፊስካል እና የገንዘብ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ በማድረግ፣ ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበት እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ፕሬዚዳንቱ ታየ ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት የዋጋ ግሽበቱን ወደ 13.9 በመቶ ማውረድ መቻሉን ጠቅሰው፣ "በዚህ ዓመትም ጥረቶቻችን ቀጥለው የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አኃዝ መውረድ እንዲችል ይሠራል" ብለዋል።

ምርታማነትን በማሳደግ አቅርቦትን ለማሻሻል፤ የዋጋ ግሽበት ትንተና ዐቅምን በማሳደግ የግብይት ሥርዓትን ለማዘመን እንደሚሠራም ጠቅሰዋል።

በከተማ ግብርና፣ በሌማት ትሩፋት፣ በስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በኢንዱስትሪ የማምረት አቅም ማሳደግ የተገኙ ውጤቶችን በማስጠበቅ እና በማላቅ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር እንደሚሠራም ተናግረዋል።

መንግሥት ሁለንተናዊ የሀገር ውስጥ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚስችሉ ሥራዎችን በማከናወን፣ ለተፈጥሮ እና ለጫናዎች አይበገሬ፣ ተገዳዳሪ እና ተወደዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት እንደሚሠራም ፕሬዚዳንት ታየ ጠቁመዋል።

በለሚ ታደሰ 

#ebcdotstream #ethiopia #parliament #inflation #የዋጋንረት