በፊት ፆሙን ሲያድር የነበረው የአፋር ክልል ለም መሬት አሁን ላይ ለመስኖ ልማት እየዋለ ይገኛል።
በክልሉ የመስኖ ልማት በስፋት እየተከናወነባቸው ከሚገኝ አካባቢዎች መካከል ደግሞ የዱብቲ ወረዳ አንዱ ነው።
በአካባቢው በሜካናይዜሽን የታገዙ የግብርና ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የወረዳው የግብርና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ መሃመድ ኖራ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

በተለይም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በየዓመቱ የተተከሉ የማንጎ፣ የሙዝ ፣ የፓፓዬ እና የተለያዩ የፍራፍሬ ተክሎች ውጤት እያስገኙ መሆኑንም ነው ያነሱት።
ከወረዳው የሚሰበሰበው የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት ከአካባቢው አልፎ ለአጎራባች አካባቢዎች ገበያም እየቀረበ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የውኃ ተፋሰሶችን በመጠቀም ኢንቨስተሮች እና ከፊል አርሶ አደሮች በቆሎ፣ ጤፍ እና ስንዴ በስፋት እያለሙ እንደሚገኝም አቶ መሃመድ ኖራ ገልፀዋል።
በሁሴን መሃመድ