በገበታ ለትውልድ እና በተለያየ መንገድ የተገነቡ የቱሪዝም ፕሮጀክቶች ለሀገር ግንባታ ሰፊ አበርክቶ እየተወጡ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል።
ገበታ ለትውልድ ለቱሪዝሙም ሆነ ለሀገር ግንባታ የሚሰጠው ፀጋ ላቅ ያለ መሆኑንም ነው ሚኒስትሯ የገለጹት።
ከዚህ ቀደም በቱሪዝም ዘርፉ ያልተጠቀምናቸው እና ተሸፍነው የቆዩ ስፍራዎችን በመግለጥ ለቱሪዝሙም ሆነ ለሀገር ግንባታ እንዲውሉ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሶማሊ ክልል የተገነባው የሸበሌ ሪዞርት ካልተጠቀምንባቸው እምቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ ተደማሪ የቱሪዝም አቅም መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡
ስፍራው ባህልና እሴት የተገለጠበት መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ፤ ከተፈጥሮ ጋር የተዋሀደ ስለመሆኑም አያይዘዋል ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በወንጪ፣ በጎርጎራ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪስት አገልግሎት መስጫዎች በርካታ ጎብኚዎችን እያስተናገዱ መሆኑም ተመላክቷል።
በሜሮን ንብረት