Search

ኢትዮጵያን ከኋላ ቀርነት ለማላቀቅ ፀጋዎቿን ይበልጥ በትብብር ማልማት ያስፈልጋል– በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አዳቶ

ማክሰኞ መስከረም 27, 2018 118

ኢትዮጵያ የውጪውን ዓለም እያማተርን ሳትሆን ያላትን እምቅ ሀብት በማስተባበር ከኋላ ቀርነትን የምናላቅቃት ባለፀጋ ሀገር ናት ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚዳት ጽ/ቤት ኃላፊ እና የፐብሊክ አድሚኒስትሬሸን እና ማኔጅመንት ምሁር የሆኑት አየለ አዳቶ ገለፁ።
አንድነትን መሰረት ያደረገ ጠንካራ ሥራ ከድህነት ለመውጣት ወሳኝ መንገድ መሆኑንም ነው ያነሱት።
 
በቅርብ ያየናቸው የሕዳሴ ግድብ ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ምርት እና የተለያዩ ግዙፍ የልማት ሥራዎች እንዲሁም ወደብን የተመለከቱ እና ተስፋ ሰጪ ለውጦች ኢትዮጵያን በመደመር መንፈስ ውጤታማ ማድረግ እንደሚቻል ያሳዩ ናቸው ብለዋል።
በመደመር መንግሥት መፅሐፍ እንደሰፈረው ፈጠራን በማስፋፋት ፣ በአግባቡ ጊዜን በመጠቀም እና ወደ እድገት ጎዳና በቀጥታ በመቀላቀል የኢትዮጵያን ልማት ማቀላጠፍ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል።
ለዚህም ሁሉም ዜጋ ለጋራ ሰላም እና እድገት በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
በሴራን ታደሰ