Search

የአምራች ዘርፉን አቅም ማሳደግ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም - የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ

ማክሰኞ መስከረም 27, 2018 114

የአማራ ክልላዊ መንግሥት የትኩረት መስክ አድርጎ እየሰራባቸው ከሚገኙ ዘርፎች አንዱ የአምራች ዘርፉ መሆኑን የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ ገለፁ።
ቢሮው በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ዙሪያ ከፋይናንስ፣ ከመሰረተ ልማት እና ከሰለጠነ የሰው ኃይል አቅራቢ ተቋማት እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
 
የቢሮው ኃላፊ እንድሪስ አብዱ ፤ የክልሉን ፀጋዎችን በማልማት እና አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገጥሟቸውን ችግሮች በመፍታት ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉን የአምራች ኢንዱስትሪ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና ሌሎችንም አንኳር ጉዳዮች ለማሻሻል የሚረዳ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ መኖሩንም አስታውሰዋል።
በስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት በ2017 ዓ.ም በክልሉ የነበሩትን 45 ሺ 606 አምራች የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን በ2027 ዓ.ም ወደ 146 ሺ 660 ለማሳደግ ታቅዷል።
 
በሳሙኤል ወርቃየሁ