ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ድርድርን ማጠናቀቋን ተከትሎ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሸቀጦች ዘርፍ የንግድ ትግበራዋን በይፋ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ውሀብረቢ እንደገለጹት ፤ የመጀመርያው የንግድ ልውውጥ በምስራቅና በደቡብ አፍሪካ አገራት ላይ ትኩረት ያደርጋል።

ነፃ ንግድ ቀጣና ንግድ ማስጀመሪያው ላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በየብስ ትራንፖርት ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ወደ ደቡብ አፍሪካ ይላካል ብለዋል፡፡