ሰባተኛው ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና ሥነ-ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።
በእውቅና ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የመደመር መንግሥት በችግር የማይታጠር እና በመፍትሔ የሚሻገር መሆኑን ተናግረዋል።
ለትጋት በመጨከን በአርዓያነት የሚመራ መንግሥት መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት።
ችግሮች ቢፈጠሩም ለችግሮች እጅ ባለመስጠት መፍትሔ እያፈለቁ መጓዝ የመደመር መንግሥት መገለጫ መሆኑን ገልጸው፤ ጩኸት አያቆመንም ክብርም አያዘናጋንም ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምረን የምንፈፅም፤ አልመን የምንተኩስ፤ ተናግረን የምንተገብር እና በቃላችን ልክ የምንገኝ መንግሥት ለመሆን እየተጋን እንገኛለንም ነው ያሉት።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ