Search

ከሚገጥሙን ፈተናዎች ዕድሎችን ፈልቅቀን እያወጣን እንሰራለን እንጂ አንቆምም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ መስከረም 28, 2018 118

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማፋጠን፤ ከሚገጥሙን ፈተና እና ተግዳሮቶች ዕድሎችን ፈልቅቀን እያወጣን መስራት እንጂ መቆም የለብንም ብለዋል።

ኢትዮጵያን  በትብብር፣ በሕብረት እና በመተጋገዝ  ካለችበት ደረጃ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ለማሸጋገር በትጋት መሰራት እንዳለበትም ነው ያነሱት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) "የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማየት ሁላችንንም ያብቃን፤ እኔ እንደማይ አምናለሁ ያመነ ከእኔ ጋር ይጓዝ" ሲሉም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለሚያደርጉ የውጭ ኩባንያዎች እና የውጭ ዜጎች ይበልጥ ትርፋማ እንዲሆኑ እና ከኢትዮጵያ ኩባንያዎች ጋር እንዲዋሀዱ በትኩረት ይሰራልም ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የኢትዮጵያ መንግሥት በኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና በኢንቨስትመንት ቦርድ በኩል ልዩ  ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል።

በሔለን ተስፋዬ