ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የነበረንን ቆይታ አጠናቅቀን ወደ አዲስ አበባ በመመለስ የሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ እና የልዑካን ቡድናቸውን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብለናል ብለዋል።
የሁለቱ ሀገራትን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ለማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብሮችን ለማጎልበት ጠንካራ ፍላጎት አለን ሲሉ ገልፀዋል።
በመሆኑም እነዚህን የጋራ አላማዎች ለማራመድ የሚጠቅሙንን ሰፊ አድማስ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።