በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተካሄደው 7ኛው የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና እና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ይበልጥ እንድንሰራ የሚያበረታታን ነው ሲሉ ተሸላሚ ግብር ከፋዮች ተናገሩ።
የፕላቲንየም፣ የወርቅ እና የብር ደረጃ ሽልማት የተሰጣቸው ታማኝ ግብር ከፋዮች፤ ግብርን በወቅቱ እና በታማኝነት መክፈላችን ጥቅሙ ለጋራ ነው ብለዋል።

ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ግብርን በታማኝነት በመክፈል የበኩላችንን እየተወጣን እንገኛለን፤ ይህንንም አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
የእውቅና እና የሽልማት መርኃ ግብሩ ይበልጥ ጠንክረን በመሥራት ተጨማሪ ግብር እንድንከፍል የሚያነሳሳ ነው ብለዋል ተሸላሚዎቹ።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ