የእንስሳት ማደሪያ ከሰው መኖሪያ ተለይቶ የተሰራላቸው፣ ዘመናዊ ማብሰያ፣ የፀሐይ ኃይል እና የስልክ መስመር የተገጠመላቸው፣ ዘመኑን የዋጀ መፀዳጃ ቤት ያላቸው የገጠር መንደሮች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተገንብተዋል።
እነዚህን ዘመናዊ የገጠር መንደር ቤቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ዘመናዊ ቤቶቹ የአኗኗር ዘዬን ለማሳደግ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀው፤ ሁሉም አቅም ያለው አካል የገጠር ዘመናዊ መንደር ግንባታን በማገዝ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ኩባንያዎች፣ ግለሰቦች እና ዲያስፖራዎች በገጠር ቤት በመገንባት የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የዘመናዊ መንደሮቹ መስፋፋት የገጠር ነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ ለማሻሻል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ተግባር የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ዜጋ ተሳትፎ የሚጠይቅ እንደሆነም አሳስበዋል።