ለታማኝ ግብር ከፋዮች የሚሰጠው የእውቅና እና የሽልማት መርኃ ግብር ላይ የተሸላሚዎች ቁጥር ከዓመት ዓመት ቁጥራቸው ከፍ እያለ መጥቷል ሲሉ የገቢዎች ሚንስትር አይናለም ንጉሴ ተናግረዋል።
ከሚጠበቀው አንፃር አሁንም የሚቀር ገቢ ቢኖርም በተከታታይ በተሰሩ ሥራዎች በ2017 በጀት ዓመት ከ900 ቢሊዮን ብር በላይ ከግብር መሰብሰቡን ሚኒስትሯ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።
ይህም ሰርተው ካተረፉት ለሀገራቸው ልማት የሚያበረክቱ ታማኝ ግብር ከፋዮች እየበዙ መምጣታቸውን ያሳያል ሲሉ አንስተዋል።
ከግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ ጋር ተከታታይ ውይይቶችን በማድረግ እና የጋራ አሰራርን በመከተል ተጨማሪ ውጤት ለማስመዝገብ ጥረት እንደሚደረግም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
በ2018 ዘመናዊ የአሰራር መንገዶችን በመተግበር በፌዴራል ደረጃ 1.28 ትሪሊዮን ብር ግብር ለመሰብሰብ አቅደናል ሲሉም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል። 
በሃብተሚካኤል ክፍሉ
#EBC #ebcdotstream #tax
 
                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                            