መልካም ጅማሯችን ላይ ትብብርን መጨመር የኩራት ምንጮች መሆንን እና በሀገር መስራትን የሚያለማምድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
ዓባይን መገደባችን እና ፕሮጀክቶችን መጀመራችን ይበል የሚያሰኝ ስኬት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስኬቱ በእያንዳንዱ ሰው ቤት ውስጥ ሊገለጥ ይገባል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአርሶ አደሩ ሕይወት ተሻሽሎ ማየት የእርካታ ምንጭ ነውና፣ ተጋግዘን እጅ አጠር የሆኑ ሰዎችን በመደገፍ ኑሯቸውን እናሻሽል ሲሉ ተናግረዋል።
አያይዘውም ይህ ሲሆን የኢትዮጵያ ብልፅግና ወደ ታሰበለት የከፍታ ደረጃ ይደርሳል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ የገጠር መንደሮችን ለአርሶ አደሮች ባስረከቡበት ወቅት፤ አርሶ አደሩ ዘመኑን የዋጀ መፀዳጃ ቤት፣ ሶላር እና በጓሮው ሰፊ የአትክልት ስፍራ ማየቱ ደስታን እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።
በሴራን ታደሰ
 
                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                            