የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ባውሚት ኦስትሪያ የ3ዲ ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ፈጽመዋል።
ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማልና የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ አርትነር ተፈራርመዋል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል በዚሁ ወቅት፤ የወቅቱ የከተሞች ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ከመሰረቱ ለመቅረፍ ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ቤት ከመገንባት ወደ ማምረት የሚያስችለውን የ3ዲ ኮንክሪት ቴክኖሎጂን ትግበራን በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ ከባውሚት ኦስትሪያ ጋር እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡
 የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ እንደገለፁት፤ የ3ዲ ቴክኖሎጂ ቤትን በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት በአጭር ጊዜ በማቅረብ የኢትዮጵያን የቤት አቅርቦት ከመሰረቱ እንደሚቀይረው ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡
የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ እንደገለፁት፤ የ3ዲ ቴክኖሎጂ ቤትን በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት በአጭር ጊዜ በማቅረብ የኢትዮጵያን የቤት አቅርቦት ከመሰረቱ እንደሚቀይረው ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡  
የኮርፖሬሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አማኑኤል አያሌው ስምምነቱን አስመልክቶ ለኢቢሲ ዶትስትሪም እንደገለፁት ኩባንያው የሚያስገባቸው የ3ዲ ቴክኖሎጂዎች በቅርቡ ውደ ሀገር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ገብተው ተከላው ይከናወናል፡፡
በስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያው የሙከራ ቤቶች ግንባታ በአጭር ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወኑም አንስተዋል፡፡
ባውሚት ኦስትሪያ የቦታ ርክክብ አድርጎ በአንድ ዓመት ውስጥ በተከታታይ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ከቤቶች ኮሮፖሬሽን ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱንም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
የ3ዲ ግንባታ ቴክኖሎጂን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ባውሚት ኦስትሪያ፤ የግንባታውን ዘርፍ በማቀላጠፍ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ተናግረዋል፡፡
በመሐመድ ፊጣሞ
 
                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                            