ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ማጠናቀቋን ተከትሎ የመጀመሪያ ምርቷን ወደተለያዩ ሀገራት በዛሬው ዕለት መላክ ጀምራለች።
በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመርኃ ግብሩ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ስጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በየብስ ትራንስፖርት ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ወደተለያዩ ሀገራት ተልከዋል።
የምርቶቹ መዳረሻዎች ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ መሆናቸውን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ላይ ተናግረዋል።
በብሩክታዊት አስራት