Search

የጋላፊ ጉምሩክ ጣቢያን ያዘመኑት የካርጎ ጭነት መከታተያዎች

ዓርብ መስከረም 30, 2018 66

ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የጭነት ተሽከርካሪዎች በብዛት በሚተናገዱበት የጋላፊ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የጭነት ተሽከርካሪዎች መከታተያ ሲስተም (ካርጎ ትራኪንግ ሲስተም) ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
በጋላፊ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የገቢና ወጪ ትራንዚት የሥራ ሒደት አስተባባሪ አቶ ብርሐኑ ፀጋዬ ፤ በእያንዳንዱ የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚደረግ የካርጎ መከታተያ በመኖሩ ይህንን መከታተያ ለማበላሸት መሞከር ያስጠይቃል ይላሉ።
በዚህም መሰረት ከተመደበበት መስመር ወጥቶ ከ70 ሜትር በላይ የተጓዘ ተሽከርካሪ ሲገኝ፤ ሲስተሙ በዋናው መስሪያ ቤትም ሆነ በቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ላይ በሚገኙ መከታተያዎች ምልክት እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
የጉሙሩክ ፈጣን ምላሽ ሰጪ አካላት እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ የኮንትሮባንድ መከላከልም በሚደርሳቸው መረጃ አማካኝነት ጭነቱን በመከታተል ለመቆጣጠር እንደሚችሉም አቶ ብርሐኑ ገልፀዋል።
በተጨማሪ በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጣቢያ መግቢያ እና መውጫ ላይ የተገጠመው “ስማርት ጌት” የተሰኘው የመቆጣጠሪያ ሲስተም እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የገባበትን ጊዜ እንዲሁም የጭነት አይነቱን በተመለከተ ለቀጣይ የክትትል ሒደት አመቺ በሆነ መንገድ መረጃ እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡
 
በንፍታሌም እንግዳወርቅ