Search

ዘመን ባንክ የአንድ አክሲዮን ትርፍን ወደ 68.3 በመቶ ማሳደጉን አስታወቀ

ቅዳሜ ጥቅምት 01, 2018 53

ዘመን ባንክ አሲዮን ማኅበር ከፍተኛ የፋይናንስ አፈፃፀም በማስመዝገብ የአንድ አክሲዮን ትርፍን ወደ 68.3 በመቶ ማሳደጉን አስታውቋል።

ባንኩ የባለአክሲዮኖች 17ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እያካሄደ ነው።

የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር በዚሁ ወቅት፥ ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 8.9 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቀዋል።

ባንኩ የአንድ አክሲዮን ትርፍን ወደ 68.3 በመቶ ማሳደጉን እና የባንኩ አጠቃላይ ሀብትም 88.6 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጸዋል።

አክለውም፥ ጊዜውን እየቀደምን የምናከናውቸው ተግባራት ለወደፊቱ ዝግጁ እንድንሆን አስችለውናል፤ ወደ ካፒታል ገበያ ኢንቨስትመንት ባንኪንግ እና ሌሎች ስትራቴጂያዊ ተግባራት ለመግባት ወሳኝ መሠረት እየጣልን ነው ብለዋል።

ዘመን ባንክ የአገልግሎት አድማሱን እያሰፋ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ 132 ቅርንጫፎችን ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በወይንሸት ደጀኔ

#ebcdotstream #zemenbank #dividends