በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሠፋ የተመራ የልዑካን ቡድን በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የተሠሩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኘ ነው።
የልዑካን ቡድኑ የባህር ዳር ከተማ የአንድ መሶብ አገልግሎት ማዕከል፣ የጣና ዳር መናፈሻ የኮሪደር የልማት ሥራዎች እና የውስጥ ለውጥስ አስፓልት መንገዶች እንዲሁም የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመጎብኘት የልምድ ልውውጡ ተካሂዷል።
የልምድ ልውውጡ የሁለቱን ከተሞች ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።
በተስፋሁን ደስታ