ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው አካላት ከኪሳራ ወደ ትርፍ ከማሸጋገራቸው ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገባቸውን የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ጠንካራ የኢኮኖሚ ለውጥ መምጣቱን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ማሻሻያው በተለይ እንደ መንግሥት የልማት ድርጅቶች ያሉ ተቋማት ውጤታማ የሆኑበት ነው ብለዋል።
ከኢኮኖሚ ማሻሻያው ወዲህ በበጀት የሚሠሩ የልማት ሥራዎች፣ የመደበኛ ወጪ ውጤታማነት እንዲሁም የፐብሊክ ፋይናንሱ ዕድገት ተጨባጭ ለውጥ ማሳየቱንም አንስተዋል።
የፕላን እና ልማት ሚንስትሯ ፍፁም አስፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ማነቆ ሆኖ የቆየውን እይታ እንደቀየረ እና አዲስ የዕድገት መንገድን እንዳመለከተ ተናግረዋል።
የሕዝቡን ጥያቄ መሰረት ያደረገው ማሻሻያው በተለያዩ ዘርፎች ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገቶች ማስመዝገብ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ መሆኑንም ሚንስትሯ ገልፀዋል።
በሴራን ታደሰ
#EBC #EBCDOTSTREAM #Economicreform